በማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

This is the heading
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.
- ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የሚካሄዱ ጥረቶችን ማስተባበር፣
- የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶችን ማካሄድ፣ ፕሮግራሞችን መቅረጽ፣
- ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚመለከት ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲዘረጋ መስራት፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዱ ስልጠናዎችን መስጠትና አውደ ጥናቶችን ማካሄድ፣ ተገቢውን የድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ አማራጭ የድጋፍ ስልቶችን መቀየስ፣
- የማህበራዊ ጉዳይ ፖሊሲዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ መስራት፣
- የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ይወገዱ ዘንድ የማህበረሰቡን ጥረት ማስተባበር፣
- በገጠርም ሆነ በከተማ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ውስጥ በቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መረጃ የመለየት፣ የማደራጀት፣ ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ስራ መስራት፣
- የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ተቋማትን የማቋቋምና ውጤታማ ማድረግ፤