Mission

በሴቶች፣ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ላይ ጉዳት እየደረሱ ያሉ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ የተዛቡ አመለካከቶችና የማህበራዊ ችግር ተጋላጭነትን ለማስወገድ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችና ስልጠና መስጠት፣ ሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ተደራጅተው ለመብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው እንዲታገሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን በመዘርጋት እና የዜግነት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማሳደግ  በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ለሚገኙ ህጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣

 

እንዲሁም በሚወጡ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና በሚዘጋጁ እቅዶች ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥና የፈጻሚ ተቋማትን አቅም መገንባት ነው፡፡

Scroll to Top