በህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

This is the heading
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.
- በህጻናት መብትናሁለንተናዊ ደህንነት ዙሪያ የወጡ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የህግ ማእቀፎችንና ስምምነቶችን ተግባራዊ/ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤
- በህጻናት መብትናሁለንተናዊ ደህንነት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፤ የግንዛቤና ንቅናቄ ፕሮግራሞችን ማካሄድ፤ የህጻናት መብትናሁለንተናዊ ደህንነትን ለማስከበር የሚረዱ የፖሊሲ ሃሣቦችን ማመንጨት/ግንዛቤ መፍጠር፤
- የህፃናትን የልደት ምዝገባ ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር መዘርጋትና ማስተባበር/ መደገፍ፤
- ከዘረመል /DNA/ ምርመራ ጋር ተያይዞ አቅም የሌላቸው እናቶት ድጋፍ የሚያገኙበትን አሰራር በመዘርጋት ህፃናት በህግ አባትነትን የማወቅ መብት ማረጋገጥ፤
- በልዩ ልዩ ምክንያቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙና ጥቃት ለሚደርስባቸው ህፃናት አገልግሎት የሚሰጡ የአንድ መስኮት እና የተሃድሶ መስጫ ማዕከላትን መደገፍና ማጠናከር፤ መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መስራት፤
- በየደረጃው የህፃናት ፓርላማዎች፣ ልዩ ልዩ ክበባትና ሌሎች አደረጃጀቶች እንዲቋቋሙ መደገፍና ማስተባበር፤ በእነዚህ አደረጃጀቶችና ልዩ ልዩ መድረኮች የሚኖራቸውን ተሳትፎ ማሳደግ፣
- የህፃናት ፓርላማ ተወካዮችን የማሳተፍ ልምድ ለማሳደግ የሚያስችሉ የምክክር ፕሮግራሞች ከአስፈፃሚና አካላትና ከክልል የህዝብ ምክር ቤቶች ማካሄድ፤
- ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ የህፃናት በዓላትን እንዲከበሩ ማድረግ/ማስተባበር፤
- የህፃናት ጤና፣ ስርዓተ-ምግብና የቅድመ ማነቃቂያ አገልግሎት እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ ማድረግ፤
- ልዩ ፍላጎት ስላላቸው ህፃናት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን የተዛባ አመላካከት ለመቀየር የሚያስችል ቀጣይነት ያላቸው የግንዛቤና የንቅናቄ ስራዎችን መስራት፣
- የህፃናት ማቆያዎች በሴክተር ተቋማት፤ በልማት ድርጅቶች እና በማህበረሰብ ደረጃ እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ መደገፍና ማስተባበር፤
- ለሕፃናት የተለያዩ ስነ ልቦናዊና ማሕበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ ማሳደጊያዎች፣ ማዕከላት፤ ሌሎች ለሕፃናት ምቹና ተስማሚ አገልግሎቶች እንዲቋቋሙ /እንዲጠናከሩ ማድረግ፤
- በህፃናት አያያዝና አስተዳደግ ዙሪያ በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ መልካም ልምዶችንና ተሞክሮዎችን መቀመርና ማሰፋፋት፣
- በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ቤተሰቦች አማራጭ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ የሚሳተፉበትንና በማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞች ተጠቃሚነት የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት፣
- ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ ፕሮግራም
- መልሶ የማቀላቀልና ዳግም የማዋሃድ ፕሮግራም
- የፎስተር /ሞግዚት ቤተሰብ ክብካቤ
- የጉዲፈቻ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ/ ፕሮግራሞችን እንዲስፋፋና እንዲጠናከሩ ማድረግ፣
- ሌሎች አማራጭ የህጻናት ክብካቤ አገልግሎቶች ከተዳሰሱ በኃላ አማራጭ ከጠፋ ህጻናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ማሳደጊያ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ