ሴቶችን ለመሪነት ማዘጋጀት ላይ ትኩረት መደረግ አለበት።

ሴቶችን ለመሪነት ማዘጋጀት ላይ ትኩረት መደረግ አለበት።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በባሕር ዳር ከተማ ባካሄደው የክልል ሴት መሪዎች ፎረም ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ሴቶችን ለመሪ እጩነት ማብቃት እና ማዘጋጀት ላይ ምክክር አድርጓል።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ እና የክልሉ ሴት መሪዎች ፎረም ሠብሣቢ ብርቱካን ሲሳይ በክልሉ የሚገኙ ሴቶች በሚኖራቸው የፖለቲካ ውክልና ላይ ለመምከር ጉባኤው መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኀላፊዋ ቢሮው የሴቶችን የፖለቲካ ውክልና ማሳደግ ላይ ልዩ ትኩረት ሲሰጥ መቆየቱንም አስረድተዋል። ከዩኤን ውመን ጋርም በመተባበር በተለይም ተተኪ ሴት መሪዎችን ለማፍራት ሰፊ ሥራዎች መሥራታቸውን ወይዘሮ ብርቱካን ተናግረዋል።

ነባር መሪዎችን ከአዳዲስ መሪዎች ጋር በማገናኘት እንዲሁም ችግር ላይ ያሉ ሴት መሪዎችን ከአሠራር እንዳይወጡ የሴቶች ፎረም በማዘጋጀት ድጋፍ ሲደረግ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

የክልሉ ሴት መሪዎች ፎረም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እና የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች አባል መኾናቸው በፎረሙ ብዙ ተስፋዎች እንዲኖሩት ማድረጉን ኀላፊዋ ገልጸዋል።

በመጭው ምርጫ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚመረጡ ሴቶችን በማብቃት እና በማዘጋጀት የተሠሩ ሥራዎችን እና በቀጣይ መሠራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደተደረገም ተመላክቷል።

ወይዘሮ ብርቱካን እንዳሉት የክልሉ መንግሥት የመልሶ ማደራጀት ሥራ ላይ ሲኾን በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የሴቶች ውክልናን ለማሳደግ ታቅዷል።

ይህ ዕቅድ የብልጽግና ፓርቲ ያወጣውን ዝቅተኛ 30 በመቶ እና ከፍተኛ 50 በመቶ የሴቶች መሪነት ውክልናን ለማሳካት ያለመ ነው። ይህም ሴቶች በቁጥራቸው ልክ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያገኙ መንገድ ይከፍታል።

የኤጅ የፕላስቲክ ቧንቧ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ አሥኪያጅ እና የክልሉ ሴት መሪዎች ፎረም ዋና ጸሐፊ ወለላ መብራቱ በበኩላቸው የፎረሙ ዋና ዓላማ ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ብቻ ሳይኾን በበመሪነት ቦታ ላይ ያሉትንም መደገፍ መኾኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ በሁሉም የክልሉ ዞኖች እና ወረዳዎች ሴቶችን በማብቃት ወደ ወደ መሪነት እንዲመጡ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top