የአብክመ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በደቡብ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የእብናት ወረዳ የሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከመሰከረም 10/01/2017 ዓ .ም ጀምሮ የአዳጋ ምላሽ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ የማሰጀመሪያ ኘሮግራም ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።
ስልጠናውን የሚሰጡት የተለያዩ ልምድና ዕውቀት ባላቸው የቢሮው የዩኒሴፍ አስተባባሪ በአቶ እሱባለው በላይ ሲሆን ፣
ሠልጣኞችም በቆይታቸው የተሻለ ግንዛቤ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስልጠናውም ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
መሰከረም ፡ 10/01/2017 ዓ.ም
ባህር ዳር


