የጡት እብጠት

ጡት የተገነባው/የተሰራው ከብዙ መዋቅሮች እንደ ስብ፣ከወተት ማመንጫ ፣ከዕጢዎች እና አያያዝ ህብረ ህዋሶች ነው ፡፡

በነዚህ መዋቅሮች ላይ የሚከሰቱ ችግሮች የጡት እብጠት ያስከትላሉ ፡፡

የጡት እብጠት ምልክቶቹ፦ የጡት መጠን መጨመር ፤ጡት ሲነካ ህመም ፤ ጡት ላይ ያሉ የደም ስሮች ከወትሮው በተለየ መልኩ መታየት ፤የጡት መክበድ፤ ብብት አካባቢ ህመም ፤የጡት ቆዳ ቀለም መቀየር ፤ህመም ስሜት መኖር፤ መቅላት ፤ማሳከክ እንዲሁም መቁሰል የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ለጡት እብጠት ተጠቃሽ መንስኤዎች ፦የቅባት አለርጂ፤ የጡት ማስያዣ መጥበብ እና አለመመቻቸት፤ ከባድ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ፤ ኢንፌክሽን፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት ፤ ሆርሞን የሚቀይር ማንኝውም መድሃኒት የጡት እብጠት ሊያስከትል ይችላል።

የሰውነት ለውጦች ፤ጉርምስና ፣ የወር አበባ እና ማረጥ የሰውነት የሆርሞን መጠን ይቀይራሉ።

በነዚህ ጊዜዎች የሚፈጠር የጡት ህመም የተለመደ ሲሆን የጡት ጉዳትና የጡት ካንሰር በሚኖርበት ወቅት ሙሉ የጡት እብጠት ሊታይ ይችላል ።

ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲታዩ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል ።

መስከረም; 10/2017 ዓ/ም

ምንጭ፤- ከአብክመ ጤና ቢሮ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top