በግምገማ መድረኩ ባለፋት ወራት በፕሮግራሙ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮች በከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የተጠቃለለ ሪፖርት በቢሮው የዩኒሴፍ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ዜና ማርቆስ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ከተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች መካከልም የፕሮግራም ከተሞች በጋራ ተገናኝተው መገምገማቸው ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ለመ እጥረቶችን ለይቶ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና በቀሪ ወራት ክፍተቶችን በመሙላት ከነበረው የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ትልቅ ልምድ አግኝተንበታል፤
የህጻናትን ጥቃት ለመከላከል እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ህጻናትና ሴቶችን ለይቶ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለማድረግ ቢሮው የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኞችን በመቅጠር አሰልጥኖ ወደ ስራ በማሰማራቱ ከአድሎ የጸዳና ትክለኛ ተጋላጭን ለይቶ ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ፤ የማህበራዊ ዘርፍ ሰራተኞች ለመሰገኑ ይገባል ፤ የህጻናት ጥቃት ከመከላከል አኳያ ከተማ አስተዳደሮች ከሚመለከታታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክረው ማስቀጠል ይገባል ያሉ ሲሆን
ከክልል የፍትህ አካላት የመጡ ተሳታፊም የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም ማንኛውም በህጻናትና ሴቶች ዙሪያ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች ዙሪያ በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎናችሁ ነን ጠይቁን ብለዋል።
በቢሮው የህጻናት መበብትና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ፣ በቢሮው የፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ አስማማው እንዳለው እንዲሁም የዩኒሴፍ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዜና ማርቆስ መድረኩን የመሩት ሲሆን በማጠቃለያም ፕሮግራሙ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ባለ ማህበረሰብ ውስጥ የሚተገበር በመሆኑ ተግባራትን ለማከናወን ምቹ ሁኔታዎችን ሳንጠብቅ ማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ተግባራትን ልናከናውን ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠቃሏል።


