የአብክመ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዩኒሴፍ ከታቀፉ የልጅነት ጋብቻ ይቁም ፕሮግራም ከሚተገበርባቸው ወረዳዎች ለተውጣጡ ቡድን መሪዎች ፣ባለሙያዎችና አመቻቾች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችንና በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል በማህበረሰብ ውይይትና የወንዶች አጋርነት ማንዋል ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው ተገኝተው ስልጠናውን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በቢሮው የህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ዩኒሴፍ በክልሉ በ16 ወረዳዎች የልጅነት ጋብቻ ይቁም ፕሮግራም ዘርግቶ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጦች መኖራቸውን አንስተው እንደ አገር የተቀመጠውን ፍኖተ ካርታ እውን ለማድረግ የተለያዩ ማስፈጸሚያ ማንዋሎች ተቀርጸው ወደ ስራ ከገቡት መካከል የማህበረሰብ ውይይት ማንዋልና የወንዶች አጋርነት ማንዋል አንዱ አካል መሆኑን በመግለጽ ፣

የስልጠናው ዋና አላማ ሰልጣኞች በማወያያ ማንዋሉ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡና ወደ መጡበት ማህበረሰብ ሲመለሱ የአመቻችነት ስራቸውን በተገቢው መንገድ በመምራት በጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከል ማህበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት ነው ብለዋል።

ስልጠናው በሁለት ቡድን ተከፍሎ በቢሮው ከፍተኛ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ ሲሆን ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቆይ ይሆናል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top