.የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት በመንግስት ቁርጠንነት ከፌደራል እስከ ቀበሌ በመንግስት የሚመራና ትልቅ ለውጥ እያሳዬ ያለ ፕሮግራም በመሆኑ በ 2022 ዓ/ም የስርዓተ ምግብ እጥረት /መቀንጨርን ለመከላከል/ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን ፣ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም የልማት ህብረትን በማጠናከር በቀሪ አመታት ከአሁኑ በተሻለ መልኩ በመስራት በክልላችን በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎችን ከስርዓተ ምግብ እጥረት ነጻ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተገጸ፡፡

የአብክመ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር በሰቆጣ ቃልኪዳን በሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ፣ ሥርዓተ ፆታና እኩልነት ፤ በልማት ኅብረት አደረጃጀት እና አሰራር ማዕቀፍ ዙሪያ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ዞኖችና ወረዳዎች ለተውጣጡ ለዞን ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ለወረዳ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ስልጠናው በአማራ ክልል የሰቆጣ ቃል ኪዳን የማህበረሰብ አቀፍ የተግባቦት አማካሪ በሆኑት በአቶ ጋሻው አዳነ ስለ ስርዓተ ምግብ ምንነት ፣ የልማት ህብረት ማስፈጸሚያ ሰነድ በቢሮው የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ ደስታ ፈንታ እንዲሁም የስርዓተ ፆታ ምንነት፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት ፣ ንግድ ስራ ዕቅድ እንዲሁም የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም አሰራር በክፍሉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞችም ለስራችን መሳካት ትልቅ ግብዓት ያገኘንበት ስልጠና ነው በማለት አሁን ክልላችን ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ስራውን ለማስፈጸም የበጀት እጥረት ተግዳሮት ሆኖናል ብለዋል፡፡
የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዝና ጌታቸው በተነሱ ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በ2022 ዓ/ም በክልላችን ስርዓተ ምግበን ለማረጋጥ የሴቶች ልማት ህብረትን ማጠናከር፣የአካባቢ ጸጋዎችን መጠቀም፣ ማህበረሰቡ ስለ ስርዓተ ምግብ ያለው አመለካከት መገንባት ፣ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በመስራት እንዲሁም ሞዴል የሆኑ ቤተሰቦችና የልማት ህብረቶችን ተሞክሮ በመቀመር ለሌሎች ማጋራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡