“ከ‎መቸውም ጊዜ በላይ በጠንካራ ቅንጅት ድጋፍና ክትትል ለተቋሙ ደንበኞች ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መስራት ይጠበቃል::”

“ከ‎መቸውም ጊዜ በላይ በጠንካራ ቅንጅት ድጋፍና ክትትል ለተቋሙ ደንበኞች ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መስራት ይጠበቃል::” ከሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ

‎የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በ2018 በጀት አመት በ1ኛው ሩብ አመትን ዕቅድ አፈፃፀም ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ገምግመዋል፡፡

‎በዕለቱም በ2018 በጀት አመት በ1ኛው ሩብ አመት የተከናወኑ አበይት ተግባራት የተከናወኑ አበይት ተግባራት በቢሮው እቅድ ዝግጅት ፥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ብርሃኑ አለሙ አማካኝነት ቀርቧል ።

‎የቀረበውን ሪፖርት ላመሰረት በማድረግ በተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች፣ አሰተያየቶችና ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በተነሱት አሰተያየቶችና ሀሳቦች ላይ በቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጧል።

በሩብ አመቱ በተለይ ተቋማት አካተው ከመተግበር አኳያ፣ ከቅንጅታዊ አሰራር አኳያ፣ በሴቶችና ህጻናት የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመከላከል አኳያ በርካታ ተግባራት የተፈጸሙ ቢሆንም የተቋሙ ደንበኞች ካለባቸው ዘርፈ ብዙ እና ውስብስብ ችግሮች እንዲሁም ከሚሹት ድጋፍ እና ከወቅታዊ ሁኔታው አንጻር ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ከተሳታፊዎችም ከአመራሮችም በትኩረት ተመላክቷል፡፡

በመጨረሻም የማጠቃላያ ሀሳብ የሰጡት፤ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ እንደገለጹት ክልላችን የ25 አመት አሻጋሪ እቅድ አቅዶ ለክልሉ ህዝብ ሰላም መስፈን እና እድገት በተለየ ትኩረት እየሰራ ባለብት በዚህ ወቅት ተቋሙ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጋር ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር በተለየ ድጋፍና ክትትል ለሴቶች፣ለህፃናት፣ ለአረጋዊያን፣ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተጋላጭ የህ/ሰብ ክፍሎች መብትና ደህንነት መጠበቅ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀውታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top