ዓለም አቀፉ የአረጋውያን ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ በዓልበዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ “ለአረጋውያን ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኀላፊነታችንን እንወጣ በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።
የአብክመ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ክብርት ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በመክፈቻ ንግግራቸው መልዕክታቸው አረጋውያን አገርን በነጻነት ያቆዩ የዳበረ ዕውቀት ባለቤት ፣በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ሀገራቸውንና ማህበረሰባቸውን ያገለገሉ የአገር ባለውለታ ናቸው በማለት
የበዓሉ መከበር ዋና ምክንያት ሀረጋውያን በዋጋ የማይተመን የዕውቀትና የጥበብ ባለቤት በመሆናቸው ፣ተንከባካቢ የሚያስፈልጋቸው በሙያቸው አቅማቸው በሚፈቅደው በቀሪ ዘመናቸው ስራ በመስራት የሚችሉ መሆናቸውና ካላቸው አገራዊ አበርክቶ አንጻር ትኩረት ዕውቅና በመስጠት በቀሪ ዘመናቸው ኢኘኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን መንግስተና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች ከአረጋውያን ጎን እንዲሆኑና ለአረጋውናን ቀሪ ዘመን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው ብለዋል።
በዓሉም የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ክላስተርቋሚ ኮሚቴ የተከበሩ ወ/ሮ አበራሽ ታደሰ፣ የአማራ ክልል አረጋውያን ማህበር ፕሬዝዳንትን አቶ አምሳሉ ማዕዛን ጨምሮ የክልል ተቋማት ከፍተኛ የስራ አላፊዎች፣የክልልና የዞን የአረጋውያን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎች ፣የዞንና የከተማ አስተዳደር የሴቶ፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዎች ፣አጋር አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የመወያያ ሰነድ በአብክመ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሆኑት በወ/ሮ ንጹህ ሽፈራው እየቀረበ ይገኛል።
በዕለቱም በአረጋውያን ዙሪያ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ቢሮዎች የዞንና ከተማ አስተዳደሮች አረጋውያን እንዲሁም ለአጋር አካላት የዕውቅና መርሀ ግብር የሚካሔድ ይሆናል::
መስከረም 28/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር




