በ2017 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በተዘጋጀው ክልላዊ የሽልማት እና የዕውቅና መርሐ ግብር ቢሮው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 113 ሴቶች ለእያንዳንዳቸው 5ሺ በጠቅላላ 587ሺህ ብር እና ለ3 አካል ጉዳተኞች ለእያንዳንዳቸው 5ሺ እንዲሁም ከቸሻየር ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ ብርድልብስ ፣ አንሶላ ፣የልብስ ሻንጣ እና ከኢሲዲዲ በተገኘ ድጋፍ የአይነ-ስውራን የገንዘብና የቁሳቁስ ሽልማት ሰጥቷል ።
በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ላመጡት አንድ ሴት እና አንድ አካል ጉዳተኛም ለእያንዳንዳቸው የታብሌትና የዋንጫ ሽልማት ተሠጥቷል ።
በተጨማሪም ከዋግኸምራ ዞን ወደመፈተኛ ማእከሏ በመሄድ ላይ እያለች በጥይት የመቁሠል አደጋ ደርሶባት ጉዳቷን ተቋቁማ የመግቢያ ውጤት ላስመዘገበችው የጽናት ተምሳሌት ሴት ተማሪ 50,000 ብር ተሰጥቷል።
ባጠቃላይ ቢሮው በጥቅሉ ከ750 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሽልማት በገንዘብና በቁሳቁስ ሰጥቷል። ።





