የአብክመ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ከምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዊ ብሄረሰብ ዞን ፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን ፣ከሰሜን ጎጃም ዞን ስር ከሚገኙ 38 ወረዳዎች ለተውጣጡ እና ምንም አይነት ስልጠና ላላገኙ የህፃናት መብትና ድህንነት ባለሙያዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙብት ከየካቲት 21/2017 ዓ ም ጀምሮ ሰልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።
የቢሮው የህፃናት መብትና ደህንነት ማሰጠበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሻግሪ ዘውዴ እንደገለፆት የአእምሮ ጤና የሰነ-ልቦነና ማህበራዊ ድጋፍ ለህፃናት እና በተሻሻለው የህፃናት ድጋፍና እንክብካቤ አማራጭ ዙሪያ ላይ እና በተያያዥ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ ለወረዳ የህፃናት መብትና ደህንነት ለአዳዲስና ለነበር ባለሙያዎች ለተከታታይ ቀናት ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።
በዕለቱም ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአብክመ ሴቶች ፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዝና ጌታቸው እንደ ገለጾት የዚህ ስልጠና ዋና አለማ አሁን ላይ ባለንበት ሁኔታ ላይ ሁነን ስንመለከት በበረካታ ችግር ውሰጥ ላሉ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናትና የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ከፋ ማህበራዊ ችግር እንዳይገቡ የወረዳ ባለሙያዎች በውቀት ላይ የተመሰረተ ምላሽ ለመሰጠትና ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናትን መረጃዎች በትክከል ለማግኘት እና በስልጠናውም የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ታሰቦ የተዘጋጀ ሠልጠና ነው በማለት አብራርተዋል።
ስልጠናውን የሚሰጡት የቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች ሲሆን ፣ ሠልጣኞችም በቆይታቸው የተሻለ ግንዛቤ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የካቲት 21/ 2017 ዓ ም
ባህር ዳር



