በአማራ ክልል በተለያዩ ኹነቶች ሲከበር የቆየው የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት “ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትን እና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ መልእክት በባሕር ዳር እየ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡

በበዓሉም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአብክመ ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የተለያዩ ሴት አደረጃጀት ኃላፊዎች የክልልና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
የአብክመ እሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊነት ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውሴቶች የህብረተሰቡን ግማሽና በላይ እንደሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ቢያመላክቱም በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የነበረውን የተዛባ የስርዓተ ፆታ አመለካከት እንቅፋት እንደሆነ በመጥቀስ ቢሮው የሴቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለያዩ ምክንያቶች ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶችና ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚመለከት ቢሮው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉን አንስተው ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁለንተናዊ ደህንነት አጋር ድርጅቶችም ሆነ ማንኛውም አካል ለዜጎች የዜግነት ግዴታውን ይወጣ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
ወ/ሮ ብርቱካን አያይዘውም ትውልድ መቀጠል ሀገር መቀጠል መልማት ማደግ መለወጥ የሚቻለው ሠላም ሲኖር ስለሆነ በማህበራዊ መስተጋብር ላይ ካላቸው ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ኃላፊነትና ተሠሚነት አንፃር ሴቶችና አረጋዊያን እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ከትውልድ ትውልድ እየተሻጋገሩ አብረውን የመጡ እሴቶቻችን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማድረግ ከልጅ እስከ አዋቂ ሠላም የሚወድ፣ ለሠላም የሚተጋ ትውልድ /ማህበረሰብ ግንባታ ላይ ጉልህ ሚና ለሠላም መስፍን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአብክመ ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በበኩላቸው ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ማብቃት ያስፈልጋል የበቃች ሴት ቤተሰቧን፣ ማህበረሰቧንና አገሯን መምራት ትችላለች፤ ሴቶች የእችላለሁ መንፈስ ይዘው ለአላማቸው የጸኑ መሆን አለባቸው፤ በተለያዩ ዘርፎች ስኬት ላይ የደረሱ ሴቶች ሌሎች ሴት እህቶቻችንን ካለባቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር እንዲወጡ መስራት ይጠበቅብናል ተብለዋል።
ክቡር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁላችንም በዓል ከማክበርና አስቦ ከመዋል በዘለለ የሴቶችን አቅም በጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት የትምህርት ተደራሽነትን ማሳደግ ፣ በበቂ ሁኔታ በተቋማት እንዲሁም በፖለቲካዊ ተሳትፎ እንቅስቃሴያቸው ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ፣እኩልነትንና ፍትሀዊነትን ማረጋገጥ ከኛ ይጠበቃል በማለት ወደፊት የመጡ ሴቶች ይበልጥ እንዲጠነክሩ በማድረግ፤ ሌሎች ሴቶችም በተሰማሩበት መስክ ውጤታማ እንዲሆኑና ወደፊትም እንዲመጡ እገዛ በማድረግ ፡ በተለያዩ ምክንያቶች መብትና ደህንነታቸው እንዳይጠበቅ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዳይረጋገጥ እድሉ የተነፈጋቸው ሴቶችንም በማየት ካሉበት ሁለንተናዊ ተግዳሮት በማውጣት መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ክቡር ርእሰ መስተዳድሩ አያይዘውም በተለያዩ ምክንያት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሁን ካለባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማውጣት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበራዊ የኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በበዓሉም በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ውጤታማ ለሆኑ ሴቶች እና የሴቶችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ለሚገኙ ድርጅቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡