የአብክመ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በደቡብ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የእብናት ወረዳ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአዳጋ ምላሽ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ የማሰጀመሪያ ኘሮግራም እና በተያያዥ ርዕሰ ጎዳዬች ላይ ትኩረት አድርጎ ከመስከረም 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናውን የሰጡት በቢሮው የማህበራዊ ጥበቃ የዩኒሴፍ አስተባባሪ በአቶ እሱባለው በላይ እና ከዩኒሴፍ ኢቲዪጵያ ባህር ዳር ቅርጫፍ በመጡ በአቶ አበበ አዲሰ ሰልጠናው ተሰጧል ።
ስልጠናውም ፦ ስለ ፕሮግራሙ ምንነትና አስፈላጊነትን በተመለከተ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፋሎች ወይም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አዳጋዎች በከፋተኛ ችግር ውሰጥ ያሉ የማህበረሰብ ከፋሎችን የአዳጋ ምላሽ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑንም ከአሰልጣኞች ተገልፆል።
እንዲሁም በዚሁ ፕሮግራም ለታቀፉ የሚችሉ የማህበረሰብ ክፍሎች እነማን እንደሆኑ በጋራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተጠቃሚዎችን መለየት እንዳለባቸው እና በተያያዡ ርዕሰ ጉዳዪች ላይ ስልጠና ተሰጧል።
በክልላችን በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በከፍ ችግር ውሰጥ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የአዳጋ ምላሽ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ ለማድረግ ግንዛቢ መሰጠቱ የተሸለ ስራ ለመስራት ያግዛል በማለት ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በተሰጠው ሠልጠና ላይም አሰተያየቶችና ሀሳቦች ተነስተዋል ፣ በተነሶት ሀሳቦችና አሰተያየቶች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ ፣ የቢሮው የማህ/ደ/ማስ ዳይሮክትሬት ዳይሬክተር አቶ በላይነው ፀጋ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኙተው እንደገለጾት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፈሎችን ተደራሸ በማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራትና የአዳጋ ምላሽ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚዎችን በመምረጥ ወይም በመለየት የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ በተዘጋጀው ሠልጠና ላይ በንቃት መሳተፋቺሁ ለቀጣይ የተሸለ ስራ ለመስራት ያግዛል በማለት ገልፀዋል።
አያይዘውሞ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ክፋተቶችን በመምላት ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፉሎችን ድጋፋ ማድረግ አለብን በማለት ከገለጾ በኃላ ፣ በተነሶት ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተው የቀጣይ አቅጠጫዎችን በማሰቀመጥ ሠልጠናውን አጠናቀውታል።
መስከረም ፡ 12/01/2017 ዓ.ም
ባህር ዳር



