በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መከላከሉ እና ተፈጽሞ ሲገኝም ለተጠቂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ የአማራ ክልል የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር ጥምረት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና ልዩ ልዩ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉበት የሚገኘው የአማራ ክልል የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር ጥምረት መድረክ ከመስከረም 19 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የምክክር መድረኩ በሁለተኛ ቀን ውሎው የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በተገኙበት በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ውይይት አካሄዷል፡፡

በዚህ በሁለተኛው ቀን የምክክር መድረክ ላይ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ በሚደርሱ ጥቃትና እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጡ የህግ ማዕቀፎች እና አሰራሮች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የውይይት መነሻ ጹሁፎች ከፌደራል በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ቀርቧል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ በወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ አማካኝነት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በሚመለከት የክልሉን አሁናዊ ሁኔታ ፣ ጥቃትን በመከላከልና የሴችንና የህጻናትን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ አበይት ተግባራት ፣እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ ከዳኝነትና ከፍትህ አካላት ጋር በትብብር ሊሰሩባቸው የሚገቡ ነጥቦችን የሚያሳይ የውይይት መነሻ ጹሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መከላከሉ እና ተፈጥሞ ሲገኝም ለተጠቂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ የአማራ ክልል የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር ጥምረት በልዩ ትኩረት በቅንጅት መስራት የትኩረት ማእከላቸው እንደሆነ በውይይቱ ተገልቷል፡፡፡፡ መግባባት ላይም ተደርሷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top