17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ።

የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮና የአብክመ ቱሪዝም ቢሮ በጋራ በመሆን የሰንደቅ አላማ ቀንን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 04 / 2017 ዓ.ም አከበሩ።

በዕለቱም የብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ባንዲራ የመስቀል ስነ-ስርዓትም የተካሔደ ሲሆን ሰንደቅ ዓላማችን የሕብረብሔራዊነታችን የአብሮነታችን ማሳያ፣ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሉዓላዊነታችን አርማ ነው፣ ሰንደቅ አላማችን የአንድነታችን የጋራ ዓርማ፣ኢትዮጵያ ምንም እንኳ ወቅታዊ ፈተና ቢያጋጥማትም አሸንፋ ትሻገራለች፣ የሚሉ መፈክሮች ተላልፈዋል።

የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ጸጋዬ ባንዲራችን ጀግኖች አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉበት ፣የአገራችን ምልክት ፣የነጻነታችን አርማ እንዲሁም የአይበገሬነታችን ምልክት ነው ብለዋል።

ጥቅምት 04/2017

ባህር ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top