የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ2017 በጀት አመት የአንደኛው ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ መድረኩ ከሴቶች፣ ከህጻናት፣ ከአረጋውያን እንዲሁም ከአካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን የምንገመግምበትና የቀጣይ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ነው ብለዋል።

የዕቅድ አፈጻጸሙ በቢሮው የዕቅድ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ብርሀኑ አለሙ እየቀረበ ሲሆን በመድረኩ የመሞሪያ ኃላፊዎች፣የሴት አደረጃጀቶች ፣ የአረጋውያን ማህበር አመራሮች እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ጥቅምት 9/2017ዓ/ም

ባህር ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top