በጉባኤዉ ተገኝተዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ሴትች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ እንደገለጹት የህፃናትን መብትና ደህንነት በተሟላ ሁኔታ ለማስጠበቅ እያከናወናቸው ካሉ ሀገራዊ ስራዎች መካከል የህፃናት የተደራጀ ተሳትፎን ማበረታታትና ማጠናከር ነዉ ብለዋል።
ሃላፊዋ አክለዉም የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ስምምነቶች ተቀብሎ በማጽደቅ ለተግባራዊነታቸው በርካታ ሀገራዊ የአሰራር ማእቀፎቸ ተቀርፀው ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
በጉባኤዉ የአማራ ክልል ምክርቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየ፣ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ ፣ የአማራ ክልል ህጻናት ፓርላማ አፈ ጉባኤ የተከበሩ እህተማሪያም አበባው እና የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታዉ(ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የአማራ ክልል የህጻናት ፓርላማ አመራርና አባላት፣ ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል።




