ቢሮው በጎንደር ከተማ ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና ለመና እና ለካለን ብናካፍል መረጃ ማዕከላት 80 ኩንታል በቆሎና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንደገለፁት ወጣቶች አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን በመንከባከብ እያደረጉት ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ኃላፊነት ወስደው አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን በቀናነት ለሚያደርጉት የእንክብካቤ ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
ህብረተሰቡ የሚያስተባብረው ካለ ፀጋ ያለው በመሆኑ ብዙ ማገዝ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው የአካል ጉዳተኞችን ቀን በዓል ለማክበር በጎንደር ከተማ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ቢሮው ሲሰራ መቆየቱ ገልጸዋል።
ሀገር የሚያድገው ሁላችንም ሰርተን እንጅ ሰው ተመርጦ አይደለም ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአካል ጉዳተኞን ቀን በዓል አስመልክቶ የምግብ እህልና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል
ዝቀተኛ ገቢ ያላቸው የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለሁለት የበጎ ፍቃድ መረጃ ማዕከላት 80 ኩንታል በቆሎና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።
የክልሉ መንግስት የተለያዩ ኩነቶች ጎንደር ከተማ እንዲከበር ማድረጉ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ መነቃቃት የሚፈጥር ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኃላ ናቸው።
የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በጎንደር ከተማ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ህዳር 29/2017ዓ/ም የማጠቃለያ ፕሮግራም በጎንደር ከተማ በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል።


