የአብክመ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር የህጻናት ጥበቃ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን (CPIMS+) አስመልክቱ የሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በተገኙብት የዳታ ቤዝ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ውይይት አደረገ ።
በዕለቱም ተገኙተው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የአብክመ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በህፃናት ጥበቃ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመጠበቅ እና ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚረዳ አስረድተዋል ።
የሕጻናትን መብት እና ደኅንነት ለመጠበቅም ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ ይህንን ችግር በመፍታት የህጻናት ደኅንነት ጥበቃን ለማሳደግ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የጎላ ሚና እንዳለው አስረድተዋል ።
አያይዘውም የተጠናከረ የመረጃ ሥርዓት መኖር ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ድረስ ያለው የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ወጥነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው፤ ሚስጢራዊነቱ የተጠበቀ በማድረግ የህጻናቱን ተጠቃሚነት እንደሚያሳድገውም አመላክተዋል ።
በዕለቱም ተገኘተው ንግግር ያደረጉት ከዩኒሴፍ የአማራ ክልል ተወካይ ኃላፊ ዓምባነሽ ነጮ (ዶ.ር) በወረቀት የሚዘጋጀው የህጻናት ጥበቃ መረጃ ውሳኔ ለመስጠት እና ለመሥራት ያለበትን ውስንነት ገልጸዋል።
መረጃውን ለማዘመን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሃሳቡን አመንጭቶ ከክልሉ ቢሮ ጋር ለመሥራት በመቻሉ እና በጋራ ጥረት ለዚህ በመድረሱ አመሥግነዋል።
የተወሳሰበ ችግር ባለበት ክልል ውስጥ ህጻናት እና እናቶች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ያሉት ዶክተር አምባነሽ ዩኒሴፍ ለችግሮች መፍትሄ የመረጃ መሠብሠብ እና ልውውጡን ለማዘመን የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው፣ የሕጻናት ጥበቃ መረጃን ዛሬ ጀምረነዋል፤ ይህንኑ ጅምር አሠራር ሁላችንም በመንከባከብ፣ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ሁሉም ለህጻናት ድጋፍ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።
በዕለቱም የውይይት መነሻ ጾፍ ከፌደራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን ፣
የቀረበውን ጾፍ መነሻ በማድረግ አስተያየቱች ተነስተውል፤የህጻናት መረጃ የሚሠበሠበው በወረቀት ስለነበር የመረጃ ድግግሞሽ እና ምስጢር የመባከን ችግር እንደነበረው ፤ መረጃ በዘመናዊ መልኩ መሠብሠቡ እና መለዋወጡ የጠራ መረጃ ለማዘጋጀት እና ከውድመት ለመከላከል እንደሚያስችል፤ ችግሩን የቀረፈ ስልጠና በመሰጠቱ ሥራውን እንደሚያግዛቸው በመግለጽ አነስተዋል ።
በተነሱት አስተያየቶች ላይም ወይይት ከተደረገ በኃላ የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዝና ጌታቸው የህፃናትን መብት እና ደኅንነት ለመጠበቅም የህፃናት የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ማጠናከር እና ለችግር ተጋላጭ ለኾኑ ሕጻናት ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ የዳታ ቤዝ ሥርዓት መዘርጋት የሕጻናት ጥበቃ ሥርዓትን ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ አለው በማለት የማደማደሚያ ሃሳብና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀውታል፡፡
ታህሳስ፤ 05 /2017 ዓ.ም
ባህር ዳር



