ከሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ሁላችን የተሻለ ስራ መስራት አለብን ተባለ ፣/የአብክመ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ /

የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በምዕራብ አማራ ዞን በሚገኙ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ዞኖች ቡድን መሪዎች፣ የሚመለከታቸው የወረዳ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙብት የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የ5 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት በባህር ዳር ከተማ ከታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲገመግም የነበረው ተጠናቀቀ ፡፡

በተመረጡ ዞኖች በ5 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቱ ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆነ፣ እንደ አጠቃላይ በቢሮው የተከናወኖ ተግባራትን ጥቅል ሪፖርትም ቀርቧል፡፡

በቀረበው ሪፖርት ላይም የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፤ ከተነሶት መካከልም፤- የገጠር የቋሚ ቀጥተኛ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን የቤት ለቤት ጉብኝትና ድጋፍ ለማድረግ በወቅታዊ ችግር ምክንያት መቸገር ፤ በባንኮች ችግር ምክንያት የተጠቃሚዎች ክፍያ መዘግያት፤ የማህበራዊ ትስስር ተግባራትን በወቅታዊ ችግር ምክንያት ለመስራት መቸገር ፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ያለመስራት፤ በበጀት አጠቃቀም ላይ ያለው ችግር የመሳስሉት የተነሱ ሲሆነ ፤ በተነሱት ሀሳቦች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

የገጠር የቋሚ ቀጥተኛ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን የዘርፉ ፈፃሚዎች ለተጠቃሚዎች በልየታና በምልመላ ላይ በንቃት በመሳተፍ በአስከፊ የድህነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በፕሮግራሙ እንዲካተቱ የማድረግና የተጠቃሚዎች ወርሀዊ ክፍያ በተቀመጠልት ጊዜ እንዲከናወን ማድረግ ፣ ተጨማሪ ፍላጎታቸውን የመለየት፣

የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን ተጠቃሚ በማድረግና የማህበራዊ ድጋፍ አግልግሎት በመስጠት ዜጎች ወደ ከፋ ማህበራዊ ችግር እንዳይገቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትስስር መፈጠር ያስፈልጋል ተባለ ፡፡

የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ንጽህ ሽፈራው በማጠቃለያው ላይ እንደገለፁት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሸ በማድረግ ወደ ከፋ ማህበራዊ ችግር እንዳይገቡ የህብረተሰቡን የጥገኝነት ስሜት በማስወገድ በራሳቸው እንዲተማመኑ ማድረግ እና ከተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የነበሩ ክፍተቶችን መሞላት አለብን በማለት ገልፀው፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀውታል።

ታህሳስ 12/ 2017 ዓ.ም

ባህር ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top