በዕለቱም የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዝና ጌታቸው ዛሬ ከዚህ የተገኘነው በተባበሩት መንግስታት ስነ ህዝብ ፈንድ ፕሮግራም/UNFPA /በፕሮግራሙ የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም በመገምገም ልምድ የምንለዋወጥበት፣ ያጋጠሙ ችግሮችን ለይተን የምናይበትና ለቀጣይ የተሻለ ውጤት የቀጣይ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ነው ብለዋል።
የፕሮግራሙ ወረዳዎች እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ያቀረቡ ሲሆንአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የUNFPA ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ መለሰ ተረፈ የክልሉን የተጠቃለለ ሪፖርት አቅርበዋል።
በቀረበው ረፖርት ላይም ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ከተነሱ ሀሳቦች መካከልም ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ሆኖም ግን በሚፈለገው ልክ ውጤት አልመጣም ፣ ለፕሮግራሙ ማሳለጫ የተገዙ ቁሳቁሶች እንዲሁም የሚሰጡ ገንዘቦች አላማቸውን እንዳይስቱ የማያቋርጥ ድጋፍና ክትትል ያስፈልጋል፤ የልጅነት ጋብቻን ለመከላከል ዋናውና ቁልፍ ተግባር ማህበረሰባዊ የሆነ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ላይ ልንሰራ ይገባል የሚሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን
በተነሱ ሀሳቦች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡ ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ ጥምረቶችን፣የሴቶች የልማት ህብረቶችን በማጠናከር ፣ ከሀይማኖት አባቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የልጅነት ጋብቻን እና ሌሎች ጥቃቶችን ለመከላከል ፣ ነጻ ቀበሌዎችን ለማብዛት እንዲሁም ከአሁን ቀደም ነጻ የሆኑትን ለማጽናት በተገቢው መንገድ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በአማራ ክልል በተባበሩት መንግስታት ስነ ህዝብ ፈንድ ፕሮግራም/UNFPA / አስተባባሪ አቶ ጌቱ የተገኙ ሲሆን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይዘዋቸው የሚመጡ ፕሮግራሞች የመንግስትን ክፍተት በመሙላት ማህበረሰባዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲሆን ውጤቱ የሚለካውም በሚመጣው ውጤት ነው፤ የፕሮግራሙን አላማና ግብ በሚገባ ተረድቶ በዕቅድ የተመራ ስራ መስራትና ጠንካራ የሆነ የሪፖርት ግንኙነት ያስፈልጋል በማለት UNFPA ህጻናት ከልጅነት ጋብቻ ተጠብቀው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና የነገ ተስፋቸው ብሩህ እንዲሆን ከመንግስት ጎን በመሆን እየሰራ የሚገኝ ነው ብለዋል።
ታህሳስ14/2017 ዓም


