የአብክመ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ለታቀፉ ዞኖችና ወረዳዎች ለመጡ ከፕሮግራሙ ፎካሎች ጋር ከስርዓተ ጾታ አንጻር የፕሮግራሙ ማንዋል አተገባበር ፣ የስርዓተ ጾታ ሞዴል ቤተሰብ፣ ስርዓተ ጾታ ማካተት እንዲሁም ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠናዊ የምክክር መድረክ እያካሔደ ይገኛል::

በመድረኩ ተገኝተው ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ

የአንድ ተቋም ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው ታች ወረዳ ላይ በሚሰራ ስራና በሚመጣ ውጤት በመሆኑ የሴቶችን የህጻናትን የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋውያንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ሞዴል ቤተሰብ መፍጠር ላይ ሌሎች ተቋማት ተቋማዊ አድርገው እንዲሰሩ ከማድረክ አኳያ እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ስራ በትኩረት ልትሰሩ ይገባል፤

በአገር አቀፍ ጀረጃ በአዲስ የተደራጀው የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን የቼክሊስት አካል አድርጎ መስራትም ለስራችሁ መሳለጥ ጠቀሜታው ትልቅ በመሆኑ የቼክ ሊስታችሁ አካል አድርጋችሁ ልትሰሩ ይገባል ፤

ጀንደር ሜንስትሪሚንግና የስርዓተ ጾታ ሞዴል ቤተሰብ የተቋሙ ዋና ስራ ቢሆንም በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎች በበጀት የተደገፈ በመሆኑ ከሌሌች በፕሮግራሙ ካልታቀፉ ወረዳዎች በላቀ መልኩ ሞዴል በመሆን ለውጥ ሊያመጡ ይገባል ብለዋል።

ስልጠናው በቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል

የካቲት 18/2017 ዓ/ም

ባህር ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top