የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙብት የ2017 በጀት አመት የ6ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የካቲት 19 /2017 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ገመገመ፡፡
በ2017 በጀት አመት በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቱ የቢሮው የዕቅድ ዝግጀትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ አለሙ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ተሳታፊዎችም የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶቸን በማነሳት ሰፊ ውይይት ከተደረጎ በኃላ፤
የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በ6ወሩ የተከናወኑ ተግባራትን የጋራ በማድረግ በጥንካሬና በድክመት በታዩ ተግባራቶች ላይ ክፍተቶችን መሞላት አለብን ፤ በማለት ከገለጾ በኃላ በተነሶት ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተው ፤የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀውታል ፡፡
የካቲት፤ 19/2017 ዓ.ም
ባህር ዳር


