የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመል ሶማቋቋም ፕሮግራም / 3R-4-CACEP / በ2017 በጀት አመት ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ከ20 የፕሮጀክቱ ወረዳወች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሰሞኑን በደሴ ከተማ ገምግሟል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በአማራ ክልል በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ሀብት ፣የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ ከፍተኛ ሃብትና ንብረት መውደሙን፣ ከሀብት ንብረት ውድመት ፤ከህልፈተ ህይወት በተጨማሪ በህዝባችን ላይም ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ እና ስነልቦና ጫና መድረሱን አንስተው

ይህንን ችግር በመፍታት የክልሉ ህዝብ ከደረሰበት የስነልቦና ጫና የኢኮኖሚ ችግር ለማውጣት በልዩ ትኩረት መስራት ስለሚያስፈልግ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በማቋቋም እየተሰራ ያለው ስራ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መልሶ የማቋቋም ተግባሩን ለማከናወን ከሚያግዙ ፕሮጅክቶች መካከል አንዱ የሆነው የ3 R – 4 – CACE Project በሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በኩል የተለያዩ ጥቃቶች ለሚደርስባቸው ሴቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማስፋት እና ማሻሻል፣ ጥቃቶችን መከላከል፤ ተፈጽመው ሲገኙም መወሰድ በሚገባቸው ርምጃዎች ወይም ምላሽ አሰጣጥ ላይ የማህበረሰብን ግንዛቤ ማሳደግና የባህሪ ለውጦችን ማምጣት እንዲሁም በተቋማት መካከል ያለን ቅንጅትና ትብብርን ማሻሻል የሚሉ አላማዎችን አንግቦ በክልሉ በ 20 ወረዳዎችና 348 ቀበሌዎች በመግባት የሴቶችን ደህንነት፣ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የመድረኩ ዋና አላማም በዚህ ፕሮጀክት በ2017 በጀት አመት ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ፤ የነበሩ ጥንካሬዎችን ችግሮችን በመገምገም በቀጣይ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በማረም በተሻለ ቅንጅት ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት በልዩ ትኩረት በመስራት የሴቶችን ደህንነት ለማስጠበቅ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ልንጫወት ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ፕሮጅክቱ የሚተገበርባቸው ዞኖችና ጽ/ቤቶች የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋም ሃላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ ፎካል ፐርሰኖች የተሳተፉ ሲሆን የፕሮጀክት ወረዳዎች ያጋጠሟቸውን ችግሮች እና የተወሰዱ ርምጃዎችን እንዲሁም የመጡ ለውጦችንን እና የተገኙ ትምህርቶችን የሚያመላክቱ አፈጻጸማቸውን የሚያሳይ ሪፖርት ፣ የክልሉን የተጠቃለለ ሪፖርት ደግሞ በቢሮው የፕሮጀክቱ የክትትልና ድጋፍ ባለሙያ በሆኑት አድኖ ሊቨን ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከሪፖርቱ በፕሮጀክት ወረዳዎች በት/ቤት እና ከት/ቤት ውጭ ላሉየልጃገረድ ክበባትን እና ዘርፈ ብዙ ፋይዳያ ለውን የሴቶች የልማት ህብረትን ለማጠናከር በህይወት ክህሎት፣ጻታዊጥቃቶችን በመከላከልና ምላሽ መስጠት፣በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በሁሉም የፕሮጀክቱ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለተውጣጡ ከት/ቤት ውጭ ላሉየልጃገረድ ክበባት አመራሮች እና ሞዴል የሴቶች የልማት ህብረቶች መሰጠቱን እንዲሁም ለተለዩ ሴቶችም ስልጠና እና የቀጥታ የገንዘብ ድጋፎችን እንደተደረገ መረዳ ትተችሏል፡፡

በውይይቱ ለተነሱ ሃሳብ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የውይይት መድረኩን በመሩት በቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝና ጌታቸው እንዲሁም በሴቶች ማደራጃ ዳይሬክተር በወ/ሮ ደስታፈን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top