የማህበራዊ ጥበቃ የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋምና ሰራ ለማሰጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደረገ ፤

የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከማህበራዊ ጥበቃ ም/ቤት አባል ተቋማት መካከል የተውጣጡ 17 የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና በቢሮው ከሴቶች፣ከህፃናት፣ከአረጋዊያና ከአካል ጉዳተኞች እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የስራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙብት የማህበራዊ ጥበቃ የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋምና ሰራ ለማሰጀመር በባህር ዳር ከተማ መጋቢት 15 /2017 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል፡፡

በዕለቱም ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ንጽህ ሽፈራው እንደገለፁት የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲን በተቀናጀና ውጤታማ በሆነ አግባብ በመተግበር አጠቃላይ የህፃናትን፣ የሴቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን፤ የአረጋዊያንን እና ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ደህንነትና ዋስትና ማስጠበቅ ዋና አላማው ነዉ በማለት አብራርተዋል፡፡

በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የማህበራዊ ጥበቃ ተግባራትን ፖሊሲዉን መሰረት አድርጎ ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠርና የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞችን ማስተባበር ያስፈልጋል በማለትም አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም የማህበራዊ ጥበቃ ካዉንስል ለማቋቋም ያስፈለገዉ አዲሱን የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ለመተግበር የሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የጋራ አስተዋጽኦ አስፈላጊ በመሆኑ ፤ ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉት ተሳትፎ የተቀናጀና ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር ታስቦ ነው መድረኩ የተዘጋጀው ብለዋል፡፡

በዕለቱም ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ፤የማስፈጸሚያ ስትራቴጅ እና የማህበራዊ ጥበቃ ቴክኒክ ኮሚቴ ማቋቋምን አስመልክቱ የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያና መከ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይነው ፀጋ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በቀረበው መነሻ ኃሳብ ላይም የተለያዩ ሀሳቡና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ የአብክመ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ንጽህ ሽፈራው ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ተጠቃሚ እንዲሁኑ ማድረግና የማህበራዊ ችግርን ለመከላከል በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ የህብረተሰቡን አቅም በማጠናከር በችግር ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማህበራዊ ችግር በዘላቂነት መፍታት አለብን ብለዋል፡፡

በተነሱት ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተው፤የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀውታል።

መጋቢት 15/ 2017 ዓ.ም

ባህር ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top