Message From Bureau
የአብክመ እሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊነት ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ሴቶች የህብረተሰቡን ግማሽና በላይ እንደሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ቢያመላክቱም በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የነበረውን የተዛባ የስርዓተ ፆታ አመለካከት እንቅፋት እንደሆነ በመጥቀስ ቢሮው የሴቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለያዩ ምክንያቶች ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶችና ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ደህንነት አጋር ድርጅቶችም ሆነ ማንኛውም አካል ለዜጎች የዜግነት ግዴታውን ይወጣ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
የደረሰባቸዉ ሴቶችና ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ደህንነት አጋር ድርጅቶችም ሆነ ማንኛውም አካል ለዜጎች የዜግነት ግዴታውን ይወጣ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ
ቢሮ ኃላፊ
The Main Sectors Of Bureau
የክልሉ ሴቶች አጠቃላይ ሁኔታ
በስርዓተ ፆታ ፅንስ ሀሳብ መሰረት ሴቶች በሀገራችን ብሎም በክልላችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሰፊ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚያሳይ ሲሆን እነዚህም የማምረት ሥራ (Productive role)፣ ትውልድን እንዲቀጥል የማድረግ ሚና (Reproductive role) እና በማሕበራዊ ግንኙነቶች የመሳተፍ (Community role) ናቸው፡፡ ስለሆነም ሴቶች በሕብረተሰቡ ውስጥ ሆነው በተለያዩ የማምረት ስራዎች በመሳተፍ፣ ወልዶ በማሳደግና በመንከባከብ ትውልድን እንዲቀጥል በማስቻል እና በማሕበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባትራን በማከናወን ለልማቱ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ግምት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ በክልላችን ሴቶች በአማካኝ በቀን ከ14 እስከ 17 ስዓት በስራ ላይ እንደሚያሳልፉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሀገራችን ሴቶችን በሚመለከት የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን ለማስተካከል መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ከእነዚህ ውስጥም የተወሰኑትን ብንመለከት ሴቶችን የሚመለከቱ ዓለማቀፋዊ እና አህጉራዊ ስምምነቶች በመቀበል፣በሐገሪቱ ሕገ መንግስት ውስጥ የሴቶች መብቶች መካተታቸው፣ ሕገ መንግስቱን ተከትሎም የሴቶችን መብት ለማስከበር የሚረዱ ራሱን ችሎ የሴቶች ጉዳይ ፖሊስን ጨምሮ ሊሎች ፖሊሲዎች፣ የቤተሰብ ህግ፣የፍታ ብሔር እና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉች መሻሻላቸው ሌሎች ሕጐች፣መመሪያዎችና ደንቦች መውጣታቸው፤የሴቶችን ጉዳይ የሚከታተል ተቋማዊ አደረጃጀት በሚ/ር ደረጃ ተዋቅሮ እስከ ወረዳ ድረስ መደራጀቱ፣የሴቶች ልማት ፖኬጅ ተቀርጾ ሥራ ላይ መዋሉ፣ በተጨማሪም ለሴቶች ልዩ ድጋፍ እርምጃ (Afermative action) እየተሰጠ መሆኑ፣ ወዘተ… የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እነዚህ አውንታዊ እርምጃዎች በመወሰዳቸው በተለይ ባለፉት ዓመታት ብዙ ሊጠቀሱ የሚችሉ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሚያቅዷቸው እቅዶችና ኘሮጀክቶች ውስጥ የሴቶችን ጉዳይ አካቶ በመተግበር በኩል ያለው አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻ መጥቷል፡፡ አብዛኞቹ ቀደም ሲል በሴቶች ላይ ይፈፀሙ የነበሩ የመብት ጥሰቶች /ጐጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና ኃይል ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ ባይወገዱም በየጊዜው እየቀነሱ መጥተዋል፡፡ ሴቶች በቤት ውስጥ በሐብትና በንብረታቸው የማዘዝ ሁኔታ እና የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸው እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎና የጤና አገልግሎት ሽፋን እያደገ መጥቷል፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ሴቶች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካና በመልካም አስተዳደር፣ የተደራጀ እንቅስቃሴ በማድረግ፣ ጥያቄዎቻቸውን የማንሳት ፍላጎትና ተሳትፋቸው በተለይ የገጠር ሴቶች መሻሻሉች አሳይቷል፡፡
ይሁን እንጅ አሁንም በተዛባው የስርአተ ፆታ ግንኙነት፣ በማህበረሰቡና በራሳቸው በሴቶችም ለዘመናት ስር ሰዶ የቆየ አመለካከት በመሆኑ በቀጣይ ስራ ይጠይቃል፡፡
የክልሉ ህጻናት አጠቃላይ ሁኔታ
ህፃናት የአንድ ማህበረሰብ መሠረት እንደ መሆናቸው መጠን እያንዳንዱ አገርና መንግስት እንደ ባህሉ ሁኔታ አትኩሮት በመስጠት ሊንከባከባቸው፣ መብታቸውንም ሊያስጠብቅላቸው ይገባል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝብ ቁጥር የሚይዙት ህፃናት ናቸው፡፡ በ2016 የኢትዩጰያ ስነ-ህዝብና ጤና ቅኝት /EDHS/ ተጠንቶ በወጣው ትንበያ መሰረት በክልላችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑት ህፃናት ውስጥ ከአስሩ አንዱ ከተፈጥሮ ወላጆቹ/ቻ ጋር እንደማይኖር/ትኖር (ይህ ማለት 11,278,676 የክልሉ ህፃናት ውስጥ1,127,868 ህፃናት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ እንደሆነ) እና 7 በመቶው( 789,508 ህፃናት) ደግሞ አንድ ወይም ሁለቱን ወላጆቻቸውን ያጡ እንደሆነ ያሳያል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በማህበራዊ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ ከምትሠራባቸው ዘርፎች አንዱ የህፃናት ጉዳይ ነው፡፡ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጐች ከመሆናቸው አኳያ ሲታይ በእርግጥም የተለየ ትኩረት በመስጠት ሁለንተናዊ የሆነ ድጋፍና እንክብካቤ በመስጠት የተስተካከለ ስብዕና ይዘው እንዲያድጉና ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጐች እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፡፡
ይህንንም መሠረት በማድረግ ሀገራችን በተባበሩት መንግስታት ድርጀት በሥራ ላይ የዋለውን የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን እና የአፍሪካ የህፃናት መብትና ደህንነት ቻርተር ተቀብላ በማፅደቅ ተግባራዊ በማድረግ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህም መሠረት የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን በሀገሪቱ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን ስልት በመቀየስ በህገ መንግስቱ የህፃናት መብቶችን በማካተት፣ የህፃናት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣የቤተሰብ ህግ፣የወንጀለኛና የፍታብሔር ህጉች በመሻሻል፣ ከፌዴራል ጀምሮ በተዋረድ እስከ ወረዳ ድረስ መንግስታዊ መዋቅር በማቋቋም፣ ብሔራዊ የህፃናት ፖሊሲ፣ ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ፣ የትምህርትና የጤና ፖሊሲ የህጻናትን ጥቅም የሚያስከብሩ በማድረግ መንግስት የወሰዳቸው አበረታች እርምጃዎች በመሆናቸው ህጻናት በከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ዕድልና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በማህበረሰቡ የሚደረግላቸው ድጋፍ እና እንክብካቤ፤ የህጻናት መሰረታዊ መብቶቻቸውና ደህንነታቸው መከበር እያደገ መጥቷል፡፡
ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ ህጻናትን የነገ ሃገር ተረካቢ አድርጎ አለመመልከት፣ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ አለማድረግ፣ህጻናት ተገቢው የአመጋገብ ስርአት አለመኖር፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ከአከባቢያቸው ለቀው መሰደድ፣በበይነ መረብ(ማህበራዊ ሚዲያዎች) ጥቃት መፈፀም፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛና የጎዳና ተዳዳሪነት፣ በህፃናት የሚፈፀሙ ጥቃቶች አሁንም የሚስተዋሉ ችግሮች በመሆናቸው በቀጣይ አጠናክሮ መስራትን ይጠይቃል፡፡
የአረጋዊያን አጠቃላይ ሁኔታ
በሀገራችንም ሆነ በዓለም ደረጃ የከተሜነት እና የኢንዱስትሪ መስፋፋት እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማደግ የሰው ልጅ የአኗኗር ዘይቤ እንዲዘምን አድርጓል፡፡ በዚህም የሰዎች አማካይ የመኖሪያ ዕድሜ ጣሪያ ከፍ በማድረጉ የአረጋውያን ቁጥር በየአመቱ እንዲጨምር አድርጓል፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሠረት ዕድሜአቸው 60 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ በዓለማችን የሚገኙ አረጋውያን ቁጥር እ.ኤ.አ. በ1950 200 ሚሊዮን፣ በ2000 590 ሚሊዮን እንደ ነበረና በ2050 ደግሞ 2.1 ቢሊዮን እንደሚደርስ ተተንብዩዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የአረጋውያን ቁጥር በ1999 ዓ.ም በህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ መሰረት 3,568,810፣ እንደ ማዕከላዊ ሲታስቲክስ 2022 ትንበያ መሰረት 5,329,180 የነበረ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የአገሪቱ ህዝብ 4.8% እና 5.06% እንደቅደም ተከተላቸው የሚወክል ነበር፡፡
የክልላችን አረጋውያን በተመለከተ ደግሞ በ1999ዓ.ም ሕ.ቤ.ቆ መሰረት 1,029,000 አረጋውያን በአማራ ክልል የነበሩ ሲሆን የጠቅላላ ህዝቡን 5.9% እንደሚሸፍን እና 89.2% አረጋውያን ደግሞ በገጠር እንደሚኖሩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንደ አማራ ክልል ፕላን ቢሮ 2017ዓ.ም ትንበያ መሰረት 1,466,543 አረጋውያን በክልላችን ያሉ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው ህዝብ 6.14% እንደሆነ መረጃዎች ያሳያል፡፡
አረጋዊያን የራሳቸው የሆኑ መሰረታዊ መብቶች እና ፍላጎቶች አሏቸዉ፡፡ ከእነዚህም መካከል የምግብ፣የመጠለያና የሕክምና አገልግሎቶች፣ የማኅበራዊ ዋስትና፣ የብድር፣ የትምህርትና ሥልጠና በእኩልነት የማግኘት፣በመረጡትና በሚስማማቸው አካባቢ የመኖር፣ ራሳቸውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍና የሕግ ጥበቃ የማግኘት፤ የግል እምነትን የማራመድና የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን የማግኘትና በክብር የመኖር፤ በምንም መስፈርት ልዩነት ሳይደረግባቸው በእኩልነት የመታየት እንዲሁም በራሳቸው አደረጃጀቶች እነኚህን መብቶች ማስጠበቅ የሚሉት መብቶችና ፍላጎቶች ይገኙበታል፡፡ በክልሉ ፕላን ቢሮ የአሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ እንደሚያመለክተው በክልላችን 21በመቶ የሚሆነው ህዝብ በድህነት የሚኖር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአረጋውያን ድርሻ ተወስዶ ሲታይ 307,974 የሚሆኑ አረጋውያን ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የመንግስትን እና የማህበረሰቡን ድጋፍ የሚሹ ናቸው፡፡
በመሆኑም መንግስት የነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ከልማቱ ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ በህገ መንግስቱ፣ በአፍሪካ ህዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋዊያን ፕሮቶኮል ስምምነት በአዋጅ ቁጥር 1182/2012 በማጽደቅ ወደ ስራ ተግብቷል፡፡
የአካል ጉዳተኞች ሁኔታ
በኢትዮጵያ ያለው የአረጋውያን ቁጥር በ1999 ዓ.ም በህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ መሰረት 3,568,810፣ እንደ ማዕከላዊ ሲታስቲክስ 2022 ትንበያ መሰረት 5,329,180 የነበረ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የአገሪቱ ህዝብ 4.8% እና 5.06% እንደቅደም ተከተላቸው የሚወክል ነበር፡፡
አካል ጉዳተኝነት አንደ ልዩ መጥፎ ዕድል እና የአምላክ ቁጣ ተደርጎ የሚቆጠሩበት አስተሳሰብ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ የግንዛቤና የአመለካከት ችግር በመሆኑ አካል ጉዳተኞች ፍፁም መስራት እንደማይችሉ በማሰብ አካል ጉዳተኞች ራሳቸውና ቤተሰባቸውን እንዲረዱና በልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ያልነበራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ መንግስት የነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች መብት በማስከበር በሀገሪቱ ልማት እኩል ተሣታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በህገ መንግስቱ፣ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ስምምነቶችን ተቀብሎ ከማጽደቅና በተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ከማካተት ጀምሮ የተለያዩ አዋጆችንና የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በማውጣትና የድርጊት መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
የአካል ጉዳተኞች ቁጥር በሚመለከት በየጊዜው የተለያዩ መረጃዎች ቢኖሩም እንደ ዓለም ጤና ድርጅት በሚሰጠው ግምት በአለማችን ውስጥ ካለው ህዝብ ውስጥ 15 በመቶ የሚሆነው አካል ጉዳተኛ እንደሆነ ይገለጻል፤ ከዚህ ውስጥ አብዛኛውም በታዳጊ ሀገሮች ውስጥ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ታዳጊ ሀገር እንደመሆኗ መጠን በርካታ አካል ጉዳተኛ ይገኝባታል፡፡ በኢትዮጵያ ቁጥሩ 19 ሚሊዮን የሚደርስ አካል ጉዳተኛ ያለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ 4 ሚሊዮን የሚበልጠው በአማራ ክልል እንደሚገኝ ይገመታል፡፡ ምንም እንኳ አካል ጉዳተኛ ሰዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እና በኢኮኖሚው ፣በፖለቲካው ፣በማህበራዊ እና በሌሎች ሴክተሮች ውስጥ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ቢገኙም አሁንም ካለባቸው አካላዊ፣ አእምሮአዊ ወይም የስሜት ህዋሳት እክል የተነሳ ከፍተኛ ለሆነ መድሎ ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡ ለዚህ መድሎ በዋነኛነት እንደምክንያት ወይም መነሻ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ደግሞ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለአካል ጉዳተኞች ያለው የአመለካከት ችግር እና የግንዛቤ እጥረት ነው፡፡
በመሆኑም መንግስት የነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ በባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በዚህም አበረታች ውጤቶች ተመዝገቧል፡፡ይሆን እንጂ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለአካል ጉዳተኞች ያለው የአመለካከት ችግር እና የግንዛቤ ዕጥረት ለመቅረፍ ስራዎች የሚጠይቁ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል፡፡
አረጋዊያን የራሳቸው የሆኑ መሰረታዊ መብቶች እና ፍላጎቶች አሏቸዉ፡፡ ከእነዚህም መካከል የምግብ፣የመጠለያና የሕክምና አገልግሎቶች፣ የማኅበራዊ ዋስትና፣ የብድር፣ የትምህርትና ሥልጠና በእኩልነት የማግኘት፣በመረጡትና በሚስማማቸው አካባቢ የመኖር፣ ራሳቸውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍና የሕግ ጥበቃ የማግኘት፤ የግል እምነትን የማራመድና የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን የማግኘትና በክብር የመኖር፤ በምንም መስፈርት ልዩነት ሳይደረግባቸው በእኩልነት የመታየት እንዲሁም በራሳቸው አደረጃጀቶች እነኚህን መብቶች ማስጠበቅ የሚሉት መብቶችና ፍላጎቶች ይገኙበታል፡፡ በክልሉ ፕላን ቢሮ የአሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ እንደሚያመለክተው በክልላችን 21በመቶ የሚሆነው ህዝብ በድህነት የሚኖር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአረጋውያን ድርሻ ተወስዶ ሲታይ 307,974 የሚሆኑ አረጋውያን ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የመንግስትን እና የማህበረሰቡን ድጋፍ የሚሹ ናቸው፡፡
በመሆኑም መንግስት የነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ከልማቱ ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ በህገ መንግስቱ፣ በአፍሪካ ህዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋዊያን ፕሮቶኮል ስምምነት በአዋጅ ቁጥር 1182/2012 በማጽደቅ ወደ ስራ ተግብቷል፡፡
ዜና | News
የአብክመ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር
በግምገማ መድረኩ ባለፋት ወራት በፕሮግራሙ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮች በከተማ...
Read Moreየአብክመ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዩኒሴፍ ከታቀፉ
በስልጠናው ተገኝተው ስልጠናውን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በቢሮው የህጻናት መብትና ደህንነት...
Read Moreየአብክመ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአዕምሮ ጤና
ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች ለአስከፊ ድህነት ሊዳረጉ ይችላሉ:: መሰረታዊ አጋላጭ ምክንያቶች...
Read Moreጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሃይማኖት አባቶች
በጎንደር ቀጠና የሚገኙ የአራት ዞኖችና የጎንደር ከተማ አሰተዳደር የሃይማኖት አባቶችና...
Read MoreCenter For The Disability
የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልማለት አካል ጉዳተኛ ዜጐችን በመቀበል በምርጫቸውና የአካል ጉዳታቸውን ታሳቢ ባደረገ መንገድ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች የሙያና የቴክኒክ ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ በገቢ ማስገኛ ስራዎች መሠማራት በሚችሉበት አግባብ ዝግጁና በገበያ ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያሰለጥን ተቋም ነው፡፡
.በክልላችን ብቸኛ ማዕከል ሲሆን ማዕከሉ የቋቋመበት ዋና ዓላማም በብሔራዊ ክልሉ ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኛ ዜጐች ያላንዳች ልዩነት አካላዊ ሁኔታቸውንና ፍላጐታቸውን መሰረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያም ሆነ የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠናዎችን በመስጠት አካል ጉዳተኞች የሚኖራቸውን በስራ ገበያ የመወዳደር አቅም ማጐልበት ነው፡፡
ክልሉ ውስጥ የሚገኙትን አካል ጉዳተኞች በመቀበል ፍላጐቶቻቸውንና ዝንባሌዎቻቸውን መሰረት ያደረገ፣ ቀልጣፋና ደረጃውን የጠበቀ ሙያዊ ስልጠናና የክህሎት ማበልፀግ አገልግሎት እንዲያገኙና በስራው ዓለም የሚኖራቸው የተወዳዳሪነት አቅም ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡
በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀም የኃይል ጥቃትን ለመከላከል እና በአንድ ማእከል ሁሉን አቀፍ ምላሽና አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡
በተጠቂዎች እና በህብረተሰቡ ላይ የማይሽር ጠባሳ የሚተው፣ በሀገር ልማት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም የከፋ በመሆኑ የችግሩን መሠረታዊ መንስኤዎች በማወቅ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት በማስፈለጉ፤
ሴቶችና ህፃናት በዚህ ጥቃት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀባቸው መሆኑና ከአካላዊ፤ወሲባዊ፤ሰነ-ልቦናዊጥቃቶችበተጨማሪ ለኢኮኖሚያዊጥቃቶች ተጋላጭ ከመሆናቸው የተነሳ የፍትህ ስርዓቱን ተጠቅመው መብታቸውን ለማስከበር የተለየ ጥበቃና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ፡
በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃቶችን ለማስወገድ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች /አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች እና ቻርተሮች / ቢኖሩም ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ እጥረቶች ያሉ እና ለውጥ ያልመጣ በመሆኑ
ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት፣ ለመከላከል፣ ተፈፅመው ሲገኙ ተጠቂዎች አገልግሎቱን ሳይጉላሉ በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ በማድረግ የህክምና፣ የፍትህ እና የቀጣይ ህይወታቸው ጉዳይ እልባት እንዲያገኙ ለማድረግና ወንጀል ፈፃሚዎችን በአጭር ጊዜ ተገቢውን እርምት እንዲያገኙ በማድረግ በተቀናጀ እና ሁሉን አቀፍ በሆኑ ዘዴዎች ተከትሎ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የአንድ ማዕከል የተቀናጀ የእንክብካቤ እና ፍትህ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማቋቋሙ አስፈላጊ ሆኗል፡፡
“የአካል ተሃድሶ አገልግሎት”ማለት ለአካል ጉዳተኞች አስፈላጊ የሆኑ ሰው ሰራሽ መሣሪዎችን በማሟላት የጉዳተኞችን አካላዊ ምቾት በመጠበቅ እና ስነ-ልቦናቸውን በመንከባከብ ሁለንተናዊ ተሣትፏቸውን ከፍ ለማድረግ ታስቦ በሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚከናወን ተግባር ነው፡፡
“የአካል ተሃድሶ ማዕከል“ማለት የሰዎችን የተጐዳ አካል መልሶ የማስተካከል ተግባር የሚከናወንበት፣ ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ ወይም ሰውሰራሽ እጅ እግር የሚመረትበትና አካልን የማሸት ወይም የፊዚዮቴራፒ ህክምና እና ስልጠና እንዲሁም የሥነ-ልቦና ምክር አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም ነው፡፡
በክልላችንበደሴና ባህርዳርላይ እንደሚገኙ ከላይ የተመላከተ ሲሆንየተቋቋሙበት ዋና አላማም በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ በሰው ሰራሽ አደጋና በተፈጥሮ ምክንያት የተለያዩ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከጉዳታቸው ጋር የተያያዘ ሁለንተናዊ የአካል ተሀድሶ አገልግሎቶችን ያለአንዳች ልዩነት በመስጠት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ከፍ ማድረግ ነው፡፡